የኦፕንኤአይ ቦቶች የበርካታ የአሜሪካ መንግሥት ተቋማት ድረገጾችን የደኅንነት መጠበቂያ ጥሰው ገቡ

የቻትጂፒቲ ፈጣሪ የሆነው ኦፕንኤአይ ኃላፊ ሳም አልትማን
የምስሉ መግለጫ, ኦፕንኤአይ ከቁጥጥር ውጭ የሚሆኑ የኤአይ ተግባራትን በተመለከተ አዲስ የመነጋገሪያ ማዕከል ሆኗል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የቻትጂፒቲ ፈጣሪ የሆነው ኦፕንኤአይ ቦቶቹ የበርካታ የአሜሪካ መንግሥት ተቋማትን ድረ ገጾች የደኅንነት መጠበቂያ ጥሰው መግባታቸውን ይፋ አደረገ።

የኤአይ ወኪሎች የአክስዮን ገበያን የሚቆጣጠረውን የፌደራል ተቋም ፣ የሥነ ሕዝብ ቢሮን፣ የትምህርት መሥሪያ ቤትን ጨምሮ "ከመንግሥታት፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሕዝብ እና ሌሎች ተቋማት" መረጃዎችን ለማግኘት መሞከራቸውን ኩባንያው ገልጿል።

ኩባንያው ይህን ይፋ ያደረገው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒስ የኦፕንኤአይ የኤአይ ሞዴሎች (ኤጀንቶች) በመንግሥት የሚተዳደረውንና የሕዝብ ያልሆኑ ሰነዶች የሚገኙበትን የጤና ፕሮግራም ድረ ገጽ ጥሰው መግባታቸውን ከገለጹ ከቀናት በኋላ ነው።

ከነሐሴ ወር ወዲህ ኤኤይ ለሕይወት አስጊ መሆኑን ጨምሮ የሚያስከትለውን አደጋ እንዲሁም የኤኤይ ቴክኖሎጂዎች ከሰዎች ቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል የተፈጠረው ስጋት እየጨመረ ነው።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ኩባንያው ኦፕንኤአይም በቅርቡ ባጋጠመው ክስተት የተወሰኑ መረጃዎች በኤአይ ሞዴሎች በተለይም ድረ ገጾችች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንዲችሉ በተሰሩ እና በሰለጠኑ ቦቶች መወሰዳቸውን ገልጿል። እነዚህ ቦቶች በመንግሥት እጅ የሚገኙ የማኅበረሰብ መረጃዎችን ለማሰስ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።

ሆኖም ኩባንያው የተወሰኑ ቦቶቹ ከተሰጣቸው አቅጣጫ በላይ ማለፋቸውን እና በድረገጾች ላይ ያሉ የደኅንነት መጠበቂያ ደረጃዎችን ማለፋቸውን መረዳት ችሏል።

ለአብነትም ከሥነ ሕዝብ ቢሮ (ሴንሰስ) መረጃ ለማግኘት በሚሞክርበት ጊዜ የኤኤይ ወኪሎቹ ሶፍትዌር ለሚሰሩ ሰዎች የተቀመጡ ዘዴዎችን (ቱሎችን) መጠቀማቸውን ኩባንያው ገልጿል።

ኦፕንኤአይ እንዳለው በቦቶቹ የተገኙት ሁሉም መረጃዎች የሕዝብ ናቸው።

Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ቦቶቹ የአሜሪካን የአክሲዮን ገበያ የሚቆጣጠረው እና ኢንቨስተሮችን ከሚጠብቀው ኮሚሽን ያገኙት መረጃም በኋላ ላይ በኤአይ ሞዴሎች በሌላ ድረ ገጽ ላይ ታትመዋል። ኦፕንኤአይ እንደሚለው ይህ ታስቦበት የተደረገ አይደለም።

በሌላ ክስተትም ኦፕንኤአይ የኤአይ ሞዴሎቹ ማስተላለፍ የሌለባቸውን መረጃ ማስተላለፋቸውን አርብ ዕለት ይፋ አድርጓል።

እንዲህ ያሉ ተግባራት ቢያንስ 53 ክስተቶችን ያስከተለ ሲሆን የኦፕንኤአይ ኤጀንት ከቻትጂቲፒ ተጠቃሚ ምሥል በመውሰድ ወደ ሌላ ቦታ ወስዶታል። ኦፕንኤአይ ይህ ትክክለኛ የመረጃ አጠቃቀም አይደለም ብሏል።

የተወሰኑ ድረ ገጾችን የደኅንነት መጠበቂያ እያለፉ እንደሆነም ገልጿል። ሆኖም በርካታ ድርጅቶች መረጃዎችን እንዳያወጡ እየጠየቁት ስለሆነ ሰለባ የሆኑ ተቋማትን እየለየ መሆኑን ጠቅሷል።

" ግባችን ለእያንዳንዱ ድርጅት እውነታውን ማሳወቅ እና ክስተቱን ማሳወቅ ይኖርብን እንደሆነ፤ ከሆነም መቼ ለሕዝብ ማሳወቅ እንዳለብን መለየት ነው" ብሏል።

ሁሉም ክስተቶች ወሳኝ የደኅንነት ጥሰቶች ተደርገው አለመቆጠራቸውንም ኩባንያው ገልጿል።

ኦፕንኤአይ ለእንዲህ ዓይነት ክስተቶች ይበልጥ ትኩረት መስጠት የጀመረው ሐምሌ ወር ላይ የኤአይ ወኪሎች ቡድን ያለ ፈቃድ የኤአይ አበልጻጊ ፕላትፎርም የሆነውን ሀኪንግ ፌስን ጠልፎ ከገባ በኋላ ነው።

ሁጊንግ ፌስ ስለክስተቱ ይፋ ያደረገ ሲሆን በኋላ ላይም ኦፕንኤአይ ኃላፊነቱን ወስዷል።

የኤአይ ሞዴሎቹ ላይ ቁጥጥር ማድረግ አለመቻሉ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮ እንደነበርም ይታወሳል።

የሀጊንገ ፌስ አጋር መሥራች ቶማስ ውልፍ በወቅቱ ክስተቱን "አንቂ ደውል " ብሎታል።

በቅርቡም የዓለማችን ሦስት ዋነኛ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተቋማት መሪዎች ኤአይ በሰው ልጅ ደኅንነት ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በሚለው ስጋት ምክንያት ዘርፉ እየተጓዘ ያለበት ፍጥነት መቀነስ አለበት ሲሉ ማሳሰባቸው አይዘነጋም።