BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊሰፋ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ የሚገኙት የትግራይ ነዋሪዎች
በርካታ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በ2012 ዓ.ም በተቀሰቀሰው እና ለሁለት ዓመት በቆየው ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት እንደታየው በክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የእርዳታ መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሐሙስ ሌሊት ጀምሮ በክልሉ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን የመሠረታዊ እቃዎች ዋጋም ጨምሯል።
ቀጥታ, የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን የሰላም ዕቅድ ውድቅ አደረጉ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በሰባት ቀን ውስጥ ዳግም ለመክፈት ያስችላል እንዲሁም በቀጣናው የሚካሄደውን ጦርነት ያስቆማል በማለት ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ ውድቅ ማድረጋቸውን ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ። ጋዜጣው በስም ያልጠቀሳቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣንንን በምንጭነት ጠቅሶ በኅዳር ወር ከሚካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ቀትሎ የአየር ድብደባው ሊቀጥል እንደሚችል ለረዳቶቻቸው መናገራቸውን ዘግቧል።
በትግራይ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው በህወሓት ትዕዛዝ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ
የትግራይ ክልል አስተዳደርን ተቆጣጥረው ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት የህወሓት አመራሮች በክልሉ ውስጥ ያለው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። በቀድሞ የህወሓት አባላት የተቋቋመው እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚመራው ስምረት ፓርቲም በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባጋራው መልዕክት የህወሓት መሪዎች አገልግሎቱን አቋርጠዋል በማለት ከስሷል።
በትግራይ ክልል የኢትዮ ቴሌኮም የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ
በትግራይ ክልል ከትናንት ሌሊት ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ። በኢንተርኔት ነፃነት ላይ የሚሰራው ኔት ብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም ከትናንት ሐሙስ ሌሊት ጀምሮ በትግራይ የኢንተርኔት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ መስተጓጎሉን አስታውቋል። ቢቢሲም ወደ መቀለ እና ሽሬ በኢትዮ ቴሌኮም መስመር ያደረጋቸው የስልክ ጥሪ ሙከራዎች አልተሳኩም።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሸን ሊቀ መንበር የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ውጥረት እና ወታደራዊ መካረር "እጅግ እንዳሳሰባቸው" ገለጹ። ግጭቱ "በአፋጣኝ እንዲቆምም" አሳስበዋል። ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማምሻውን ባወጡት መግለጫ፤ የመቀለ፣ የአክሱም እና ሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው፣ ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን መያዙ እና የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች መቋረጣቸው እንዳሰጋቸው አስታውቀዋል።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ሐሙስ ከሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው አረጋገጡ
ጠባቂዎቻቸው ተቀይረው፣ መኖሪያ ቤታቸው ከረቡዕ ምሽት አንስቶ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር የዋሉት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በትግራይ ኃይሎች ከቤታቸው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋገጡ። ከሐሙስ ሌሊት ጀምሮ በጄነራሉ መኖሪያ ቤት ዙሪያ የነበሩት የፀጥታ ኃይሎች ከሰዓት በኋላ "ይዘነው መሔድ አለብን፣ ታዝዘናል" ማለታቸውን ቢቢሲ ከቅርብ ምንጭ የሰማ ሲሆን፣ ሌ/ጄ ታደሰ ከቤት ሲወሰዱ ምንም ዓይነት የኃይል እርምጃም ሆነ ማንገላታት አልነበረም ብለዋል።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, “ከትብብሩ ጀርባ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን አሉበት” ጃዋር መሐመድ
ሰባት የተቃዋሚ ኃይሎች የፈጠሩትን ትብብር አስመልክቶ ቢቢሲ ከፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። በቃለ መጠይቁ ትብብሩ ሦስት ውጤቶች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከትበብሩ ጀርባ እንዳሉ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊያጠፋን ይችላል?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውሎ ከፍተኛ ጥቅምን አስገኝቷል። በዚህም ውስብስብ ነገሮችን ከማቅለል አልፎ በርካታ ተግባራትን በቀላሉ ለመፈጸም አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች የሰዎችን ሥራ እየወሰደ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቶ አሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት እየተሰማ ነው
ቪዲዮ, አነጋጋሪ የሆነው የቻይናው ፕሬዝዳንት የካይሮ ጉብኝት
የቻይናው ፕሬዝዳንት ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ግብፅ በአባይ እና በቀይ ባሕር ላይ የምታራምዳቸውን አቋሞች የሚደግፍ የጋራ መግለጫ ሁለቱ አገራት አውጥተዋል። የዓለማችን አንዷ ኃያል አገር ቻይና ይህንን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ትብብር የመሠረቱት ታጣቂ ቡድኖች አንድ የሚያደርጋቸው እና የሚያለያያቸው ምንድን ነው?
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመሥረታቸውን እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አስታውቀዋል። ይህንን ትብብር ከመሠረቱት የትጥቅ ቡድኖች መካከል የተወሰኑት በአንድ ወቅት በጠላትነት የሚተያዩ እና እርስ በርስ የተዋጉ ነበሩ። እነዚህ ትብብር መሥርተናል የሚሉት ታጣቂ ቡድኖች ባለፉት ዓመታት በጠላትነት የሚተያዩ አንዳንድ ጊዜም ግጭት ውስጥ የገቡ ነበሩ። ቡድኖቹን ምን አንድ ያደርጋቸዋል? በምንስ ይለያያሉ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ስለተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን የምናውቀው
የትግራይ የእርስ በርስ ጦርነት በፕሪቶርያ ስምምነት ከተገታ ወዲህ ከረቡዕ መስከረም 13 አንስቶ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ተቀስቅሷል። ረቡዕ ዕለት ግጭቱ ስለ መጀመሩ ይፋዊ መረጃ ቢወጣም ማክሰኞ ዕለት በትግራይ አላማጣ ከተማ ተከታታይ የድሮን እና የአውሮፕላን ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል። ግጭቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው። ስለ ግጭቱ አስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?
በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል ኃይሎች እና በትግራይ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ
ለወራት በውጥረት ውስጥ በቆየው የትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት መቀስቀሱን የህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ጦርነት መቀስቀሱ የተገለጸው ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረው በረራዎች መቋረጣቸው ከተነገረ በኋላ ነው።
የትግራይ ኃይሎች የመቀለ አውሮፕላን ማረፊያን "መቆጣጠራቸው" ከተሰማ በኋላ ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ
የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ የሚገኘውን አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸው ከተሰማ በኋላ ወደ ትግራይ በረራዎች ተቋረጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ "ለጊዜው መቋረጡን" አስታውቋል።
ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠሩ ተጠቃሽ አምስት የፖለቲካ ጥምረቶች ከምን ደረሱ?
ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ በርካታ ኃይሎች በአንድ የሚያስተሳስሯቸውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሮችን ፈጥረው ተንቀሳቅሰዋል። ከእነዚህም መካከል አገሪቱን በአዲስ መልክ ያዋቀረው እና ለረዥም ጊዜ ያስተዳደረው ኢሕአዴግ እና ከተቃዋሚዎች መካከል የበርካቶችን ድጋፍ አግኝቶ የነበረው ቅንጅት ተጠቃሾች ናቸው። እነዚህ እና ሌሎች ባለፉት አሥርታት የታዩ ስብስቦች ለምን ተመሠረቱ? ምንስ አስገኙ? ፍጻሜያቸውስ ምን ሆነ?
ጥምረት መመሥረታቸውን ስላስታወቁት ታጣቂ ቡድኖች ምን እናውቃለን?
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራውን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዓላማው ያደረገ ነው የተበላው "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመሥረቱ ይፋ ሆኗል። ይህ ስብስብ በኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑት ጀምሮ ዓመታት የሚቆጠር ታሪክ ያላቸው ቡድኖች፣ እንዲሁም በጠላትነት ይተያዩ የነበሩ ቡድኖች ያሉበት ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች ውስጥ መሠረታቸውን ያደረጉት እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ታሪካዊ ዳራ ምን ይመስላል?
ስለትብብሩ እና ስለ ቀጣይ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች ጃዋር እና ልደቱ ምን ይላሉ?
አቶ ልደቱ አያሌው እና አቶ ጃዋር መሐመድ በሰባት ታጣቂ ኃይሎች የተመሠረተውን ፀረ-መንግሥት ትብብር በተመለከተ የተለያየ አቋም አላቸው። ሁለቱም ፖለቲከኞች የትብብሩን ምሥረታ አስፈላጊነት በተለያየ አገላለፅ ቢያምኑበትም በሂደቱ፣ በትብብሩ አባላት የእርስ በርስ ግንኙነት እና በቀጣይ ውጤቱ ላይ ግን ልዩነቶችን አንፀባርቀዋል። ቢቢሲ ሁለቱን ፖለቲከኞች ትብብሩን በተመለከተ አስተያየታቸውን እንዲሰጡት ጠይቋል የጠይቋቸዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለ25 ዓመታት ያሰሯቸው የትግል ጓዶቻቸው የት ናቸው? ጥያቄያቸውስ ምን ነበር?
ኤርትራ ነጻ አገር ከሆነች ጀምሮ እየመሯት የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ የፖለቲካ ለውጦችን እንዲያካሂዱ በይፋ ጥያቄ ያቀረቡት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር አውለዋው ደብዛቸው ከጠፋ 25 ዓመታት ተቆጥረዋል። ቡድን 15 የሚባሉት ባለሥልጣናት ያቀረቡት ጥያቄ ምን ነበረ? ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሩብ ክፍለ ዘመን ያሉበት ስላልታወቁ የትግል ጓዶቻቸው ምን ይላሉ?
ፍትሕ የተጠሙ የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች አቤቱታ እና የፍትሕ ሚኒስቴር ምላሽ
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ አሰቃቂ ግፎች እና ግድያዎች ከፍተኛ ትኩረትን እየሳቡ በየጊዜው መነጋጋሪያ ሆነው ሲያልፉ ቆይተዋል። ከእነዚህ በሕዝቡ ውስጥ ቁጣን ከቀሰቀሱ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎች ተገቢውን ቅጣት አግኝተዋል ወይ የሚለው ነው? ነገር ግን በተለይ ከፍተኛ ትኩረትን ስበው የነበሩ የጥቃት እና የግድያ ወንጀሎች መቋጫቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ተድበስብስው መቅረታቸው ወይም ፈጻሚዎቹ ነጻ የሚሆኑበት አጋጣሚዎች ታይተዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በሳምንታት ኢራንን ያንበረክካል ተብሎ ስድስተኛ ወሩን በደፈነው ጦርነት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመሩ ከስድስት ወራት በኋላ፣ አጭር ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ጦርነት፣ መጨረሻው ግልጽ ያልሆነ እና የተራዘመ ሆኗል። የካቲት 21/2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነቱን ሲጀምሩ በሳምንታት ውስጥ እንደሚቋጭ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ጦርነቱ ጋብ እያለ አስካሁን ዘልቆ ተጽእኖው በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ከፍተኛ ክፍያ ከሚጠይቁት ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱ
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ተማሪ በዓመት ከሚያስከፍሉት ክፍያ አንጻር ከፍተኛ የሚባሉ ዋጋዎችን ያስቀምጣሉ። በአውሮፓውያኑ 2026/27 የትምህርት ዘመን የወጡ የክፍያ መረጃዎች እነዚህ ትምህርት ቤቶች በዓመት እስከ 37 ሺህ ዶላር በላይ ወይም ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር እንደሚያስከፍሉ ያመለክታሉ። ትምህርት ቤቶቹ እንደ ተማሪው ዜግነት፣ የክፍል ደረጃ እና የክፍያ ዓይነት የተለያየ ተመንም አላቸው።
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
ባለ ፓስፖርት አይጦች እና ስለ ቲቢ የሚመራመሩት ኢትዮጵያዊ
አይጦች በጎ ስም የላቸውም፤ ሰዎች ከቤታቸው፣ ምግብ እና የተለያዩ እቃዎች ከሚያስቀምጡባቸው ሥፍራዎች አይጦችን ለማራቅ መርዝ ወይም መጥመድ ይጠቀማሉ። በአጠቃላይ አይጦች ከጥፋት ጋር ስለሚያያዙ በበርካቶች ዘንድ የተጠሉ ናቸው። ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ምርምር የሚያደርጉባቸው ባለ ፓስፖርት አይጦች ግን ለሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው።
አጃኢብ!
በኢትዮጵያ 55 በመቶ ሴቶች ሚስትን ለመደብደብ የሚያበቃ ምክንያት አለ ብለው እንደሚያስቡ ጥናት አሳየ
በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያደረገው ጥናት አመለከተ። ሚስትን ለመምታት አሳማኝ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ብዛት ከሴቶች ያነሰ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር በ11 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
ቪዲዮ, ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች, ርዝመት 1,28
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች
ቪዲዮ, የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?, ርዝመት 1,24
የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?



